
የ፳፻፲፰ ዓ/ም ዐዲስ ዓመት የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የእንኳን አደረሰዎ መርሐ ግብር እየተከናወነ ይገኛል።
በመርሐ ግብሩ ላይ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ተሃይማኖት፣ ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ አቡነ ሳዊሮስ፣ ብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ አቡነ ዲዮስቆሮስ፣ ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ የሀገረ ስብከታችን ሊቀ ጳጳስ፣ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ምክትል ሥራ አስኪያጆች፣ የየመምሪያውና የድርጅት ሐላፊዎች፣ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የዋና ክፍል ሐላፊዎች፣ የክፍላተ ከተማ ቤተ ክህነት ሥራ አስኪያጆች፣ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የገዳማትና የአድባራት አስተዳዳሪዎች ዋና ጸሐፊዎች፣ የታላላቅ ገዳማት አባቶች፣ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን የሰንበት ት/ቤት ማደራጃ መምዘራን፣ የምስካየ ኅዙናን አገልጋዮችና የተምህሮ ማስተማር ሰንበት ትምህርት ቤት መዘምራን ፣ የጋሞ ማኅበረሰብ ኦርቶዶክሳውያን መዘምራን ተገኝተዋል።
ምንጭ ፦ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሚዲያ