” ዘይፈቅድ ይትልወኒ ይጽላእ ነፍሶ ወያጥብዕ ወይንሣእ መስቀለ ሞቱ ወይትልወኒ” ማቴ16÷24
” እኔን መከተል የሚወድ ቢኖር ራሱን ይካድ መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ ” ማቴ16÷24

ዘይፈቅድ ይትልወኒ ይጽላእ ነፍሶ ወያጥብዕ ወይንሣእ መስቀለ ሞቱ ወይትልወኒ=እኔን መከተል የሚወድ ቢኖር ራሱን ይካድ መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ ማቴ16÷24
አባ አትናቴዎስ ወልደ ጎርጎርዮስ
ዘዝዋይ ገዳም 04/11/2017
ሐምሌ 5
አምስቱ አዕማደ ምሥጢርን ያጸኑ በሕይወት የተረጎሙ
የቅዱስ ጴጥሮስና የቅዱስ ጳውሎስ የዕረፍት ቀን ነው።
በዕለተ ዕረፍታቸው የሕይወት ታሪካቸው ከፍ ብሎ ይደመጣል
ዝክረ ሞታቸው ይተረጎማል ክብራቸው ይነገራል
እግዚአብሔርን ለሚፈራ ሰው ከፊት ይልቅ የመጨረሻው እንደሚያምር በዕረፍታቸው በሚደረጉ ተአምራት ይታወቃል
የጻድቁ አባታችን የአቡነ ገብረ መንፈስቅዱስም ወርሃዊ መታሰቢያ ነው በረከታቸው አይለየን
ቅዱስ ጴጥሮስ
በግሪክጴጥሮስ በአረማይክ ኬፋ ማለት አለት ማለት ነው የቅዱስ ጴጥሮስ የቀድሞ ስሙ ስምዖን ሲሆን ጌታችን ከፋ ብሎታል።
የተወለደው ገድለ ሐዋርያት እንደሚነግረን በገሊላ ባህር ዳርቻ በምትገኘው በቤተ ሳይዳ ነው ያደገው በገሊላ ባህር አጠገብ በነበረችው ጥንታዊት ከተማ የጌታችንን ቃል ባለመስማቷ
አንቺ ቅፍርናሆም እስከ ሰማይ ድረስ ከፍ ብትይ እስከ ሲኦል ድረስ ተወሰነ ዘንድ አለሽ ከተባለች አሁን ጠፍ በሆነችው በቅፍርናሆም ነው።
ጥሪ =የጴጥሮስ መተዳደሪያ አሣ ማጥመድ ነበረ ከወንድሙ ከእንድርያስ ጋር በመሆን ከአባታቸው ጋር በገሊላ ባህር አጠገብ አሣ ኢያጠመዱ ሳለ ጌታችን ሲጠራቸው ተከተሉኝ ከአሁን በኋላ በወንጌል መረብነት ሰውን የምታጠምዱ አደርጋችኋለሁ አላቸው
አባታቸውንና መረባቸውን ትተው ተከተሉት።
ከጥሪ በኋላ ጌታችንን ተከትሎ ከዋለበት እየዋለ ካደረበት እያደረ ትምህርተ ወንጌል በተግባር የተማረ ሊቀ ሐዋርያት ለመሆን የተመረጠ ጌታችን ሰዎች እኔን ማን ይሉኛል ብሎ ሲጠይቅ አንዳዱ ኤርምያስ አንዳንዱ ኤልያስ አንዳንዱ ደግሞ ዮሐንስ መጥምቅ ይሉሃል ብለው ሲመልሱ እናንተስ እኔን ማን ትሉኛላችሁ አላቸው ቅዱስ ጴጥሮስ አንተማ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነህ አለው ጌታችንንም የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ ብፁዕ ነህ ሥጋና ደም አልገለጠልህም የሰማይ አባቴ እንጂ አንተ አለት ነህ ባንተም አለትነት ቤተ ክርስቲያንን እሰራታላሁ የሲኦል ደጆችም አይችሉአትም የመንግሥተ ሰማያትን መክፈቻ እሰጥሃለሁ በምድር ያሰርከው በሰማይ የታሰረ ይሆናል የተባለለት ታላቅ ሐዋርያ ነው።
ጌታችን እሞታለሁ አሰቀላለሁ ባለ ጊዜ ደንገጥ ብሎ አይሁንብህ አይደረግብህ በማለቱ አንተ ሰይጣን ከኔ ወግድ የተባለ
በታንኳ እየሄዱ እያለ ማዕበሉ በተነሣበት ጊዜ ጌታችን በባህሩ መካከል እየተራመደ ሲመጣ ምትሐት መስሎአቸው ሲደነግጡ
አይዟችሁ እኔ ነኝ ሲላቸው አንተ ከሆንክ ወዳንተ እንድመጣ እዘዘኝ ብሎ ጌታችን ና ብሎት በባህር መካከል እየሄደ ሳለ በመጠራጠሩ ሊሰጥም ሲጀምር ጌታን ሆይ አድነኝ ተብሎ ይጮኸል ጌታችንም ለምን ተጠራጠርክ ያለው
ሁሉም ቢክዱህም እኔ አልክድህም በማለቱ ጌታችንን ዶሮ ሳይጮኽ ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ ያለው ጌታችን ሲያዝና ሲገረፍ አላውቀውም ብሎ ሦስት ጊዜ የካደ ከዶሮ ጩኸት በኋላ ትዝ ብሎት የንስሐ ዕንባ ያነባ ሐዋርያት ነው
ከርደተ መንፈስቅዱስ በኋላ በአንድ ተቀን ሦስት ሺ ህዝብ ያሳመነና ያጠመቀ የመጀመርያዋ የሐዲስ ኪዳን ቤተ ክርስቲያን የመሠሰረተ ክርስቲያኖች በህብረት እንዲያመሰግኑ ያደረገ ሐዋርያነው ቅዱስ ጴጥሮስ በጥላው ድውይ ይፈውስ ነበረ
በመጨረሻ በሮም አደባባይ በመስቀል ሊሰቅሉት መስቀል ሲያቀርቡ እኔ እንደ ጌታዬ ተስተካክየ አህየ መስዬ መሰቀል የለብኝም ዘቅዝቃችሁ ስቀሉኝ ብሎ ሐምሌ 5 በሮም አደባባይ ዘቅዝቀው ሰቅለውት ነፍሱን ለአምላኩ ያስረከበ እኔን የሚወድ ነፍሱን ይጥላ መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ ያለውን ቃል የተረጎመ ቅዱስ ሐዋርያነው በረከቱ ትድረሰን
።።።።።።።።።።።።
ቅዱስ ጳውሎስ
የዕብራይስጥ ስሙ ሳውል ነው።
ትርጉሙ ስጦታ ነው
ጳውሎስ ማለት ንዋይ ህሩይ ማለት ነው ምርጥ ዕቃ ማለት ነው
ትውልዱ ከነገደ ቢንያም ነው
ከልጅነቱ ጀምሮ በኢየሩሳሌም በገማልያል ስር ቁጭ ብሎ ህገ ኦሪትን ተምሯል።
የጌታችን መምጣት ሞትና ትንሣኤ ባለመቀበሉ ለሕገ ኦሪት በመቅናቱ ክርስቲያኖችን ያሳድድ ነበረ
የጠራው የሐ. ሥ 9÷1 ላይ እንደተዘገበው ጌታችን ባረገ በ፰ኛ ዓመት ነው ሳውል ሳውል ለምንት ትሰድደኒ ሳውል ሆይ ለምን ታሳድደኛለህ ብሎ በመብረቅ ብልጭታ የጠራው ምርጥ ዕቃ ያደረገው ከ72 አርድእት አንዱ የሆነው ሐናንያ እኔዲያስተምረውና እንዲያጠምቀው ካደረገው በኋላ
ለሕገ ኦሪት ቀናተኛ የነበረውን ያህል ለሕገ ወንጌል አብዝቶ ቀና
በብዙ ደከመ በመንፈስ ቅዱስ እየተመራ ብዙ ሕሙማንን ፈወሰ
በቃሉ በጥላው በልብሱ አጋንንትን ያስወጣ ነበረ
በሃልና በሥልጣን ያስተምር ነበረ 14 መልዕክታትን ጻፈ
ህሙማን ወዳሉበት እየገባ እነርሱ መስሎ እንደታመመ ተኝቶ በኢየሱስ ክርስቶስ ብናምን ያድነናል አለ አንተ መጀመርያ ኪዳን አሉት በኢየሱስ ክርስቶስ አምናለሁ ብሎ ብድግ ሲል
የታመሙት ሁሉ በኢየሱስ ክርስቶስ አምነናል ብለው እንዲፈወሱ አድርጓል ለቅዱስ ጳውሎስ የተሰጠው ጸጋ ከሁሉም ይለያል
በቃል
በተግባር
በጽሁፍ በሁሉም ያስተምር ነበረ መከራ ሲደርስበት ሁሉም ነገር ለቀቀ ነው እያለ ያስተምር ነበረ ሲታሰር ሲገረፍ አላፍርበትም ያንኩትን አውቃለሁና ይል ነበረ።
ገድለ ሐዋርያት እንደሚነግረን በ69 ዓ.ም ሮም ገብቶ ስያስተምር ኔሮን ቄሣርን ተቆጥቶ አስጠሩት አለ ቅዱስ ጳውሎስ መስቀሉን ይዞ ቀረበው ንጉሡ በቁጣ በሰይፍ ቅጡት አለ
ፊቱን በመጎናጸፊያ ሸፍኖ በሰይፍ አሰይፎታል ሰማዕትነት መቀበል የ72 ዓመት አረጋዊ እንደበረ ይነገራል
እኔን የሚወድ ራሱን ይካድ መስቀሉን ይሸከም ያለውን በተግባር ተረጎመ ሐምሌ አምስት የብርሃናተ ዓለም የቅዱስ ጴጥሮስና የቅዱስ ጳውሎስ በዓለ ዕረፍታቸው ቤተ ክረስቲያን ታከብራለች
ይህንን በዓል የምናከብረው
1ኛ ጌታችን ከእኔ ተማሩ እንዳለ ከእርሱ ተምረው ለቃሉ ታምነው በቃሉ መሠረት የሕይወት ፍጻሜያቸውን ያከናወኑ ስለሆነ
2ኛ እነርሱ ከጌታ እንደተማሩ እኛም ከእነርሱ መማር ስላለብን
ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ እኔ ክርስቶስን እንደምመስል እናንተም እኔን ምሰሉ ስላለ
3ኛ በአገልግሎታችው ፍጻሜ የክብር አክሊል እንደ ተቀበሉ ሁሉ የኛም ፍጻሜ በሃይማኖት ጸንተን በበጎ ምግባር ተቃኝተን ከሆነ የምንኖረው ለእነርሱ የተሰጠ የክብር አክሊል ለኛም እንደሚዘጋጅ ስለምናምን
4ኛ የነርሱ አምላክ የኛም አምላክ ነውና እነርሱን እንዳከበረ እኛንም አክብረናል ብለን በማመን አምላከ ጴጥሮስ አምላከ ጳውሎስ አምላከ ቅዱሳን እያልን እናመሰግነዋለን በረከታቸው አይለየን
ጸልዩ በእንተ ሰላም
ስለ ቤተ ክርስቲያናችን
ስለ ሀገራችን ሰላም
ስለህዝባችን
በጭንቅ በመከራ ስላሉት
ስለ ግፉአን
ጧሪ ቀባሪ ስላጡት ሁሉ
ያለመታከት እንጸልይ
አምላካችን ክፉውን ሁሉ ያርቅልን