ነሐሴ 29.1

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኲሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ከሁለት ወራት የሰሜን አሜሪካ ቆይታ በኋላ ቅዳሜ ጳጕሜን 1 ቀን 2017 ዓ.ም ወደ መንበረ ክብራቸው ኢትዮጵያ ይገባሉ ::
የቅዱስነታቸውን በሰላም ወደ ቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ መንበረ ክብራቸው መምጣታቸውን አስመልክቶ ደማቅ አቀባበል ይደረጋል!
ቅዱስነታቸው ቅዳሜ ጳጕሜን 1 ቀን 2017 ዓ.ም ማለዳ ጠዋት ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ
ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽሕፈት ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ ፣ የሸገር ከተማና የደቡብ ምዕራብ ሸዋ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የምስካየ ኅዙናን መድኃኔዓለም ገዳም የበላይ ጠባቂ
ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ፣በክልል ትግራይ ደቡባዊ ዞን ማይጨውና የራያ ስድስቱ ወረዳዎች አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣የማኅበራት ክትትልና ቁጥጥር ማደራጃ መምሪያ የበላይ ኀላፊ፣

ብፁዓን ሊቃነጳጳሳት የቋሚ ሲኖዶስ አባላት
ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ የአዲስአበባ ፣ የሐድያና ስልጤ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ
ልብሰ ተክህኖ የለበሱ ሊቃውንት፣ካህናት ና የሰንበት ት/ቤት ወጣቶች በታላቅ መንፈሳዊ ሥርዓት ይቀበሏቸዋል ።

ከዚያም በቀጥታ ከቦሌ ኤርፖርት ወደ መንበረ ፖትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ያመራሉ!
ቅዱስነታቸው ከብጹዓን ሊቃነ ጳጳሳት ጋር መንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ሲደርሱ
ንቡረ እድ ኤልያስ አብርሃ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት በመንፈሳዊ ዘርፍ ምክትል ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ

ረ/ፕ ቀሲስ ግርማ ባቱ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ ዘርፍ ምክትል ሥራ አስኪያጅ

የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የየመምሪያውና የድርጅት ኀላፊዎች ፣ሊቃውንት ና ካህናት የመንበረፖትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ሠራተኞች፣የአዲስአበባ ሀገረ ስብከት የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች፣
የአዲስአበባ ሀገረ ስብከት አድባራትና ገዳማት አስተዳዳሪዎችና ሠራተኞች፣የሰንበት ት/ቤት ወጣቶች የገዳሟ አገልጋዮች፣ ምዕመናን ተገኝተው ቅዱስነታቸውን ወደ ቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ መንበረ ክብሮ በሰላም መጡ በማለት ደማቅ አቀባበል ይደረግላቸዋል !!!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *